መዝሙር 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞች በፊትህ አይቆሙም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ትጠላለህ። |
“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስረኞችም ጩኸት እግዚአብሔር ይላል፥ አሁን እነሣለሁ፤ መድኀኒትን አደርጋለሁ፥ በእርሱም እገልጣለሁ።”
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
ፈቃዱ አይደለምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ አንተ ግን እንደ ተሳልህ ስእለትህን ስጥ።
ክፋታቸውም ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸውና።
ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?