አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ቸል አትበል።
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ስማ።
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
ተመልከተኝ፥ ስማኝም፤ አዘንሁ፥ ደነገጥሁ፥ ተናወጥሁም፤
አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም በኢየሩሳሌም ጸሎት ይቀርባል።
በረዳታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤
መንፈስ ቅዱስም ከድካማችን ይረዳናል፤ እንግዲያስ ተስፋችንን ካላወቅን ጸሎታችን ምንድነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ስለ መከራችንና ስለ ችግራችን ይፈርድልናል።
የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”
ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፤ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት።
ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደክማለሁና ባርያህን እንደ ኀጢአተኞች ሴቶች ልጆች አትቍጠራት።”