ተቀምጠህ ወንድምህን ታማዋለህ፥ ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋትን አኖርህ።
ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤ ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥ ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።
ያለ ማስተዋል ሀብት ያካበተ ሰው እንደ እንስሳ መሞቱ አይቀርም።
ወደማልመለስበት ስፍራ፥ ወደ ጨለማና ወደ ጭጋግ ምድር፥
እፍ ብሎባቸዋልና ይደርቃሉ፥ ጥበብም የላቸውምና ይጠፋሉ።
ብራብም አልለምንህም፥ ዓለም ሁሉ በመላው የእኔ ነውና።
ሰው ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖር፥ በሁሉም ደስ ቢለው፤ የጨለማውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆናልና። የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።