ከክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ? ኀጢአት ተረከዜን ከበበኝ፤
አይተውም ተደነቁ፤ ደንግጠውም ፈረጠጡ።
እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።
ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤ ፈርተውም ሸሹ።
የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ።
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበው መጡ፤ እስራኤልንም በማሮን ውኃ አጠገብ አንድ ሆነው ተያያዙአቸው።