በኀይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትቀጠቅጣቸዋለህ።
እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።
ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፥ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
አምላካችን የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር ዘምሩለት!
በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤ የጽድቅ አምላክ እግዚአብሔር፥ ተቤዠኝ።
ለምድር ሁሉ ደስታን የሚያዝዝ፥ የጽዮን ተራራዎች በመስዕ በኩል ናቸው። የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።
እንደሰማን እንዲሁ አየን፥ በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።
በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”