ከርቤና ሽቱ ዝባድም በልብሶችህ ናቸው።
ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ
አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን፥ የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው።
አምላክ ሆይ! ዘወትር በአንተ እንመካለን፤ ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
በጨለማና በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፥
እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥ እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
ጋሻና ጦር ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
የእስራኤልም ልጆች ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ይከብራሉም ይባላል።
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንተ አይሁዳዊ፥ በኦሪትህ የምታርፍ፥ በእግዚአብሔርም የምትመካ ከሆንህ፥