አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
መዝሙር 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በእግዚአብሔርም ታመኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሩ፥ ኃጢአትንም አትሥሩ፥ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፥ ዝምም በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ትክክለኛውን መሥዋዕት አቅርቡ፤ እምነታችሁንም በእርሱ ላይ አድርጉ። |
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ጥበብን አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥ እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥ በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲፈልጉ፤
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን የምወድድ፥ ስርቆትንና ቅሚያን የምጠላ ነኝ፤ እንደ ሥራቸውም ለጻድቃን እከፍላቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።
ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አሕዛብን ያጠፉአቸዋል፤ በዚያም ይጠሩአቸዋል፤ የጽድቅ መሥዋዕትንም ይሠዋሉ፤ የባሕሩም ሀብት፥ በባሕሩ ዳር የሚኖሩ ሰዎችም ገንዘብ ይመግብሃልና፥