La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 37:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ ኀይ​ሌም ተወኝ፥ የዐ​ይ​ኖ​ቼም ብር​ሃን ፈዘ​ዘ​ብኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉ አድራጊዎች ፈጥነው ይጠፋሉ፤ ብትፈልጋቸው እንኳ አታገኛቸውም።

Ver Capítulo



መዝሙር 37:10
25 Referencias Cruzadas  

ኢዩም ጋሻ​ጃ​ግ​ሬ​ውን ቢድ​ቃ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “አን​ሥ​ተህ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው በና​ቡቴ እርሻ ጣለው፤ አን​ተና እኔ ጎን ለጎን በፈ​ረስ ተቀ​ም​ጠን አባ​ቱን አክ​ዓ​ብን በተ​ከ​ተ​ልን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተና​ገ​ረ​በት እኔ አስ​ባ​ለ​ሁና አን​ተም ታው​ቃ​ለ​ህና፤


ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙ​ዎ​ችን አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸው። እንደ አመ​ድ​ማዶ በሙ​ቀት ይጠ​ወ​ል​ጋል። ከቃ​ር​ሚ​ያው እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እሸ​ትም ይቈ​ረ​ጣል።


ወደ ቤቱም ዳግ​መኛ አይ​መ​ለ​ስም፥ ስፍ​ራ​ውም ዳግ​መኛ እር​ሱን አያ​ው​ቀ​ውም።


ስለ ምን መተ​ላ​ለ​ፌን ይቅር አት​ልም? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ስለ ምን አታ​ነ​ጻም? አሁን በም​ድር ውስጥ እተ​ኛ​ለሁ፤ በማ​ለ​ዳም አል​ነ​ቃም።”


የዱር ዛፎች ሁሉ፥ የተ​ከ​ል​ኸው የሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባም ይጠ​ግ​ባሉ።


የዱር አራ​ዊት ሁሉ፥ የም​ድረ በዳ እን​ስ​ሶ​ችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸ​ውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።


የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።


ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፤