መዝሙር 35:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአፉ ቃል ዐመፅና ሽንገላ ነው፤ በጎ ሥራን ይሠራ ዘንድ ማስተዋልን አልወደደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚያሳድዱኝ ላይ፣ ጦርና ጭሬ ምዘዝ፤ ነፍሴንም፣ “የማድንሽ እኔ ነኝ” በላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይፍንና ጦርን ምዘዝ፥ የሚያሳድዱኝን ለመቃወም፥ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና ሰይፍህን ምዘዝና “እኔ አዳኝህ ነኝ” ብለህ አረጋግጥልኝ። |
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይቀጣል።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”