ለእኔስ ሰላምን ይናገሩኛልና፥ በግርፋትም ያጠፉኝ ዘንድ ይመክራሉ።
ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ ጌታ ግን ከሁሉ ያድናቸዋል።
እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም።
ስድስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድንሃል፥ በሰባተኛውም ጊዜ ክፋት አትነካህም።
ምሕረትህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።
ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል፥
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
ይህ ሁሉ የሆነው “ከእርሱ ዐፅሙን አትስበሩ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
ነፍስህም ዛሬ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች እንዲሁ ነፍሴ በእግዚአብሔር ፊት ትክበር፤ ከመከራም ሁሉ ይሰውረኝ፤ ያድነኝም።”