ለሚፈሩት ችግር የለባቸውምና ቅዱሳን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
እርሱ በተናገረ ጊዜ ዓለም ተፈጠረ፤ በትእዛዙም ሁሉ ነገር ጸንቶ ቆመ።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
እግዚአብሔርም፥ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
አቤቱ፥ ሕዝብህን አዋረዱ፥ ርስትህንም አሠቃዩ።
ሜም። “እግዚአብሔር ያላዘዘው ይመጣል፥
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠረ፥ የሚታየውም ነገር ከማይታየው እንደ ሆነ በእምነት እናውቃለን።