“እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
መዝሙር 33:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችሁ ዘንድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤ የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ዕቅድ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዓላማውም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። |
“እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘለዓለም እንዲኖር ዐወቅሁ፤ በእነርሱም ላይ መጨመር ከእነርሱም ማጕደል አይቻልም፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል።
ቅዱስ እግዚአብሔር ይህን መክሮአል፤ የእግዚአብሔርን ምክር የሚመልስ ማን ነው? የተዘረጋች እጁንስ የሚመልሳት ማን ነው?
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።