የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን ይቅርታ ይከባቸዋል።
ሕይወቴ በመጨነቅ፣ ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ ከመከራዬ የተነሣ ጕልበት ከዳኝ፤ ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።
ተቸግሬአለሁና አቤቱ ምራኝ፥ ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ደከመ፥ ነፍሴም ሆዴም።
ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
ከአዝመራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ስለ ደረሰብኝም አስፈሪ ነገር ሁልጊዜ አለቅሳለሁ።
የሚያስተውል፥ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤ ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።
ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፤ ከመናገሬም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ፦
አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ።
ዐመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ።
እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።
በጊዜው ሁሉ ብዙ ኀዘን፥ የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለ።