ከንቱን ነገር የሚጠብቀውን ሁሉ ሁልጊዜ ጠላህ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።
እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣ “ከቶ አልናወጥም” አልሁ።
ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ “ከቶ አልሸነፍም” አልኩ።
ወጥመድ በኃጥኣን ላይ ይዘንባል፤ እሳትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፋንታ ነው።
እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥ ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
አንቺም፥ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላሰብሽም፤ ፍጻሜውንም አላስታወስሽም።
ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ በታላቅ ምሕረትም ይቅር እልሻለሁ።
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
ስለዚህም ቢሆን በብዙ ራእይ እንዳልታበይ ሰውነቴን የሚወጋ እርሱም የሚጐስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ።