በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
ክፉ ሰዎች ሲያጠቁኝና ሊገድሉኝ ሲቃጡ እነርሱ ራሳቸው ተሰናክለው ይወድቃሉ።
ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ? ከሥጋዬስ ስለምን አትጠግቡም?
“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራራላቸው፥ ሥጋውን እንበላ ዘንድ ማን በሰጠን ብለው እንደ ሆነ፥
አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
ኀጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው ምሎ የማይከዳ።
ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።
ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታዬም ነፍሴን ያድናታል።
ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው በተመለሱ ጊዜ፥ ይታመሙ፥ ከፊትህም ይጥፉ።
ስለዚህም ከእነርሱ ብዙዎች በእርሱ ይሰናከላሉ፤ ይወድቁማል፤ ይሰበሩማል፤ ይጠመዱማል፤ ይያዙማል።”