የሚያዩኝ ሁሉ ይጠቃቀሱብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ፦
ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኗልና፤ ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ ከቆመበት አይናወጥም።
የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስ ታሰኘዋለህ።
ንጉሡ የሚተማመነው በእግዚአብሔር ነው፤ የማያቋርጠው የልዑል እግዚአብሔር ፍቅር ከእርሱ ጋር ስለ ሆነም አይናወጥም።
ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፥ መርገምንም ተሞልቶአል፤
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት ጥበብን ትናገራለች።
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
ውኆቻቸው ጮኹ ደፈረሱም፥ ተራሮችም ከኀይሉ የተነሣ ተናወጡ።
ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ በጥሜም ሮጥሁ፤ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።
ፍጻሜአቸውን አውቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
በማለዳ ምሕረትህን፥ በሌሊትም እውነትህን መናገር፥
በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፤’ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው።”
ዳግመኛም፥ “እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች እነሆ፥” አለ፤ ዳግመኛም፥ “እኔ እታመንበታለሁ” አለ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።