ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ይቀበልህ።
ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ ጠፈርም የእጁን ሥራ ያወራል።
አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ያንኑ መልእክት ያስተላልፋል፤ አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀቱን ያካፍላል።
እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትንም ውኆች ለየ።
በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።”
ጐልማሶችና ደናግል፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፤
እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት።
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን ብቻ ያመሰግኑሃል፤ ከዛሬ ጀምሮ ጽድቅህን የሚናገሩ ልጆችን እወልዳለሁ።