እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
ሁልጊዜ ጌታን በፊቴ አየዋለሁ፥ በቀኜ ነውና አልታወክም።
ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።
ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል።
ለመፍረድ ዙፋኖቻቸውን በዚያ አስቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች።
እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥ ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
“በእግዚአብሔር አመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ከወደደው ያድነው።”
ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና፥ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ።
የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይውጣ።
የንጉሡንም ቍጣ ሳይፈራ፥ የግብፅን ሀገር በእምነት ተወ፤ ከሚያየው ይልቅ የማይታየውን ሊፈራ ወዶአልና።