Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ ግብጽን ለቅቆ በእምነት ወጣ፤ የማይታየውንም እንዳየው አድርጎ በመቍጠር በሐሳቡ ጸና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና፥ የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብጽን አገር ትቶ የሄደው በእምነት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የንጉሡንም ቊጣ ሳይፈራ ከግብጽ የወጣው በእምነት ነው፤ በዐይን የማይታየውንም አምላክ እንዳየው ያኽል ሆኖ በዓላማው ጸና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 11:27
27 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።


የማ​ይ​ታ​የ​ውን እንጂ የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ አና​ደ​ር​ግም፤ የሚ​ታ​የው ኀላፊ ነውና፥ የማ​ይ​ታ​የው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነው።


እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት።


እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።


እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ህም ሕዝብ ሁሉ ከዚ​ያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወ​ር​ዳሉ፤ ለእ​ኔም ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ እወ​ጣ​ለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በም​ድ​ያም፥ “ነፍ​ስ​ህን የሚ​ሹ​አት ሰዎች ሁሉ ሞተ​ዋ​ልና ተመ​ል​ሰህ ወደ ግብፅ ሂድ” አለው።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።


እና​ንተ የተ​ጠ​መ​ቃ​ች​ሁ​በ​ት​ንና ብዙ መከራ የታ​ገ​ሣ​ች​ሁ​በ​ትን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን አስቡ፤


ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።


በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና።


ከዚ​ህም በኋላ ታግሦ ተስ​ፋ​ዉን አገኘ።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


ዳዊ​ትም ስለ እርሱ እን​ዲህ አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሁል​ጊዜ በፊቴ አየ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ል​ታ​ወክ በቀኜ ነውና።


በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


ለጊዜው ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፤ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ።


እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


እንደ ዐይን ብሌን ጠብ​ቀኝ፤ በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ሰው​ረኝ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ይኸ​ውም የማ​ይ​ታይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው፥ ከፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኵር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios