በከሃሊነቱ አመስግኑት፤ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።
ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና አመስግኑት።
ስለ ታላላቅ ሥራዎቹ አወድሱት፥ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አወድሱት።
ስላደረገው ድንቅ ሥራ አመስግኑት፤ ወደር ስለማይገኝለት ታላቅነቱ አመስግኑት።
ማዳን በማይችሉ በአለቆችና በሰው ልጆች አትታመኑ።
እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል።
መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም።
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ታላቅነትህንና ኀይልህን፥ የጸናች እጅህንና የተዘረጋች ክንድህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ፥ እንደ ኀይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው?