መዝሙር 149:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተጻፈውን ፍርድ በእነርሱ ላይ ያደርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻድቃኑ ሁሉ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው። ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የደነገገውን በመፈጸም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ድልን ይጐናጸፋሉ። እግዚአብሔር ይመስገን። |
የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።