የእግዚአብሔርንም ስም ያመሰግናሉ። እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ፤
እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።
የጌታን ስም ያመስግኑት፥ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ።
ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! እርሱ አዘዘ እነርሱም ተፈጠሩ።
እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ጨለማን ታመጣለህ ሌሊትም ይሆናል፤ በእርሱም የዱር አራዊት ሁሉ ይወጡበታል።
የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዝአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ።
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ትእዛዙንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው።