የሰው ሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።
ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።
እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተመሰገነ ነው፥ ጌታ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው።
እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው! እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው!
ሕዝቅያስና አለቆቹም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።
ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው?
ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች።
መከራን ባሳየኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉንም ባየንባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለናል።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”