ከሰማይ በታች እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ የተዋቡ ሴቶች በሀገሩ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው።
መዝሙር 144:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ልጆች ኀይልህን የመንግሥትህንም ክብር ታላቅነት ያስታውቁ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻቸን በጉልማስነታቸው እንደ አዲስ አትክልት ይሁኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸንም እንደ እልፍኝ ይመሩና ያጊጡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው ጊዜ እንደ አዲስ ተክል የሚያድጉና የሚጠነክሩ ይሁኑ፤ ሴቶች ልጆቻችን ለቤተ መንግሥት ማእዘኖች ውበት እንደሚሰጡ፥ ተቀርጸው ቀጥ እንዳሉ ምሰሶች ይሁኑ። |
ከሰማይ በታች እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ የተዋቡ ሴቶች በሀገሩ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው።
ይወድድህማል፤ ይባርክህማል፤ ያባዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ፥ የመሬትህንም ፍሬ፥ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የከብትህንም ብዛት፥ የበግህንም መንጋ ይባርክልሃል።