አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለም አመሰግናለሁ።
እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣ እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ።
ስለ ጎልያድ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታዬ ዐለቴ፥ ይባረክ፥ ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር፥
መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።
ለእጆቼ ጦርነትን ያስተምራል፤ ለክንዴም የናስ ቀስት አዘዘ።
የእስራኤልንም ንጉሥ አለው፥ “እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን።” ዮአስም እጁን በቀስቱ ላይ ጫነ፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦
ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት ጥበብን ትናገራለች።
ቃላቸው ያልተሰማበት ነገር የለም፥ መናገርም የለም፥
ተራሮችና ኮረብቶች የሕዝብህን ሰላም ይቀበሉ።
ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም አንባ ነውና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
ክብርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ከእግዚአብሔርም የሚርቁ ሁሉ ያፍራሉ።
የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ጽኑ ምሽግን በሚያፈርስ በእግዚአብሔር ኀይል ነው እንጂ።