አቤቱ፥ በአዲስ ምስጋና አመሰግንሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ ከጠላቶቼ አድነኝ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ስለ ተማጠንኩ ከጠላቶቼ አድነኝ።
የቀድሞውን ዘመን ዐሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አነበብሁ፤ የእጅህንም ሥራ አነብባለሁ።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ ሰውነቴ አልቃለች፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፤
በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ሽንገላን ይታታሉና።
አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤ ገረፍኸን፥ ይቅርም አልኸን።
የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።