ያግቤጽም፥ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ ሀገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ምልክት አድርግልኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
መዝሙር 142:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎት፥ በዋሻ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት ትምህርት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ምሕረት እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ። |
ያግቤጽም፥ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ ሀገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ምልክት አድርግልኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ።
በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች ወጣ፤ በዚያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ወደዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።