Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያቤጽም “እባክህ! መባረክን ባርከኝ፤ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ፤” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 4:10
56 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


በከ​ሃ​ሊ​ነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የም​ና​ስ​በ​ው​ንና የም​ን​ለ​ም​ነ​ውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበ​ዙም ዘንድ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ ለሚ​ችል፥


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


እኔም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ጠ​ፉም፤ ከእ​ጄም የሚ​ነ​ጥ​ቃ​ቸው የለም።


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


አባ​ቶ​ቻ​ችን አን​ተን አመኑ፥ አመኑ፥ አን​ተም አዳ​ን​ሃ​ቸው።


ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።


በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለከ​በ​ሩና ቅዱ​ሳን ለተ​ባሉ የእ​ነ​ር​ሱና የእኛ ጌታ የሆ​ነ​ውን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ስም በየ​ስ​ፍ​ራው ለሚ​ጠሩ ሁሉ፥


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።


ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥


አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።”


ለስ​ሙም ዘምሩ፥ ለክ​ብ​ሩም ምስ​ጋ​ናን ስጡ።


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


እኔስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ለመ​ለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ታመ​ንሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጠ​ራሁ እር​ሱም የመ​ለ​ሰ​ልኝ እኔ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው መሣ​ለ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሆን ሰው ሆኛ​ለሁ፤ ጻድ​ቁና ንጹሑ ሰው መሣ​ለ​ቂያ ሆኖ​አል።


ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


ከዚ​ያም በቤ​ቴል ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ተራራ ወጣ፤ በዚ​ያም ቤቴ​ልን ወደ ምዕ​ራብ፥ ጋይን ወደ ምሥ​ራቅ አድ​ርጎ ድን​ኳ​ኑን ተከለ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።


ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አስ​ቀ​ድሞ ልጁን አስ​ነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ከክ​ፋ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​መ​ለሱ ይባ​ር​ካ​ችሁ ዘንድ ላከው።”


መታ​ዘ​ዛ​ች​ሁም በሁሉ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል፤ እኔም በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ናል፤ ለመ​ል​ካም ነገር ጠቢ​ባን፥ ለክፉ ነገ​ርም የዋ​ሃን እን​ድ​ት​ሆኑ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት የዘ​መ​ር​ዋት መዝ​ሙር ይህች ናት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን አውሩ።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


በዳ​ና​ችሁ ጊዜ የታ​ተ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቅዱስ መን​ፈስ አታ​ሳ​ዝ​ኑት።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


እን​ዲ​ህም አላት፥ “አን​ቺስ ብታ​ውቂ ሰላ​ምሽ ዛሬ ነበረ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን ከዐ​ይ​ኖ​ችሽ ተሰ​ወረ።


ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።


ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው።


የሱ​ሃም ወን​ድም ካሌብ የኤ​ስ​ቶ​ንን አባት ማኪ​ርን ወለደ።


ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥


ወደ አባ​ቴም ቤት በጤና ቢመ​ል​ሰኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ይሆ​ን​ል​ኛል፤


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እር​ሱም፥ “ያዕ​ቆብ ነኝ” አለው።


የመ​ው​ለ​ጃ​ዋም ወራት በደ​ረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኜ​ዋ​ለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙ​ኤል” ብላ ጠራ​ችው።


እር​ስ​ዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጸ​ለይ በዚህ በፊ​ትህ ቆማ የነ​በ​ረች ሴት እኔ ነኝ።


ስለ​ዚህ ልጅ ተሳ​ልሁ፤ ጸለ​ይ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ን​ሁ​ትን ልመ​ና​ዬን ሰጥ​ቶ​ኛል፤


በኀ​ይ​ልህ ሰላም ይሁን፥ በክ​ብ​ርህ ቦታ ደስታ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios