አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤ ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ቃል አድምጥ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞችም ሰዎች ጠብቀኝ፤
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞች እጅም ጠብቀኝ።
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
እግዚአብሔርም በሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
ለድሆች ሕዝብህ በጽድቅ ፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች አድናቸው። ትዕቢተኛውንም አዋርደው።