መዝሙር 14:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገሮችን ይሠራሉ። በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም። |
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
ኀጢአተኛ ወገንና ዐመፅ የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ በደለኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ተዋችሁት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጣችሁት።
የይሁዳም ወገኖች በእግዚአብሔር ዋሹ፤ እንዲህም አሉ፥ “እንደዚህ አይደለም፤ ክፉ ነገርም አይመጣብንም ሰይፍንና ራብንም አናይም፤
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።