እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ከመቅሠፍቱ ይቅር አለ፤ የሚያጠፋውንም መልአክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
መዝሙር 135:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፣ ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባርያዎቹንም ይረዳልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል። |
እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ከመቅሠፍቱ ይቅር አለ፤ የሚያጠፋውንም መልአክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የምትመለስ አምላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና።
ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ፤ ደስም አሰኙት፤ የእስራኤልም ልጆች ከሥቃይ የተነሣ አእምሮአቸውን አጥተው ነበር።