መዝሙር 125:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስተኞችም ሆን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን እጃቸውን ለክፋት እንዳያነሡ፣ የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች በጻድቃን ምድር ላይ የሚዳኙት ለብዙ ጊዜ አይደለም፤ አለበለዚያ ጻድቃንም ክፉ ማድረግን ይጀምራሉ። |
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
በሰው ላይ እንደሚደርሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያገኛችሁም። በምትችሉት መከራ ነው እንጂ በማትችሉት መከራ ትፈተኑ ዘንድ ያልተዋችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፤ እርሱም ከፈተና ትድኑ ዘንድ በመከራ ጊዜ ይረዳችኋል።
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።