መዝሙር 124:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን እጃቸውን በዐመፃ እንዳይዘረጉ እግዚአብሔር የኃጥኣንን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይተውምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣ በቁመናችን በዋጡን ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታላቅ ቊጣ በእኛ ላይ ተነሥተው ከነሕይወታችን በዋጡን ነበር፤ |
ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤ ከዚህ ወደዚህ አቃዳው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤ የምድር ኃጥኣን ሁሉ ይጠጡታል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።