የኀያል አምላክ መንገድ ንጹሕ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእሳትም የጋለ ነው፤ በእርሱም ለሚታመኑት ጠባቂያቸው ነው።
መዝሙር 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው። |
የኀያል አምላክ መንገድ ንጹሕ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእሳትም የጋለ ነው፤ በእርሱም ለሚታመኑት ጠባቂያቸው ነው።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋልና፥ በተዘረጋችም ክንድ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።”
“በእነርሱ ላይ እነሣለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም አጠፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።