ጐልማሳ መንገዱን በምን ያቀናል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
በኃያላን ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
በመሪዎች ከመመካት ይልቅ፥ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።
አሦርም ይወድቃል፤ የሚወድቀውም በሰው ሰይፍ አይደለም፤ የምትበላቸውም የሰው ሰይፍ አይደለችም፤ የሚሸሹም ከሰይፍ ፊት አይደለም ጐልማሶቻቸው ግን ይሸነፋሉ።
በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ፤ ጫንቃቸውንም ሁሉ አቈሰልህ፤ በተደገፉብህም ጊዜ ተሰበርህ፤ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።
አሁንም፥ “ንጉሥ የለንም፤ እግዚአብሔርን አልፈራንምና፤ ንጉሥስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።