ዓይኖችን ክፈት፥ ከሕግህም ድንቅ ነገርን አያለሁ።
መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።
መገሠጽስ ጌታ ገሠጸኝ፥ ለሞት ግን አልሰጠኝም።
በብርቱ ቀጥቶኛል፤ ነገር ግን እንድሞት አላደረገኝም።
ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
በራብ ጊዜ ከሞት ያድንሃል፥ በጦርነትም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።
ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ፤
ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን በጌታ እንገሠጻለን።
እንደማይታወቁ ስንታይ የታወቅን ነን፤ እንደ ሰነፎች ስንታይም ልባሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስንታይ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆንም አንገደልም።