ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እከፍለዋለሁ?
አምላካችንስ በሰማይ ነው፤ እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።
አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።
እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው።
“ስለ ፍርድ የሚከራከር ማን ነው? እርሱ የወደደውን ያደርጋልና።
ጨረቃን በጊዜው ፈጠርህ፤ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል። እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል።
በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐመፅ የሚከብቡኝ ጠላቶቼ በረቱ፤ ያልወሰድሁትን ይከፈሉኛል።
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!
እንግዲህ ምን ትላለህ? አንተ እግዚአብሔርን ትነቅፈዋለህን? ምክሩንስ የሚቃወማት አለን?።
እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰን በእርሱ ርስትን ተቀበልን።