Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 115:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላካችንስ በሰማይ ነው፤ እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምንን እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 115:3
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።


“እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው? እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።


እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቷል፤ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።


በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ።


በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሠኘውን ሁሉ ያደርጋል።


በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።


ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም ተቀኙ፤ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፤ ስሙ እግዚአብሔር በተባለው ፊት፣ እጅግ ደስ ይበላችሁ።


የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤ ‘ምክሬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሠኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ።


ከሕዝብ መካከል ትሰደዳለህ፤ ከዱር አራዊት ጋራም ትኖራለህ፤ እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ሁሉ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለውና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመት ያልፋል።”


የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።


“እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤


ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሠናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል።


ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እርሱ ዕቅድ፣ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ ደግሞ በርሱ ተመርጠናል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos