በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
መዝሙር 110:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ይከምራል፥ በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤ በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፤ ብዙ አሕዛብንም ይዘልፋቸዋል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍን አያነሣም፤ ሰልፍንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
ጽድቄ ፈጥና ትመጣለች፤ ማዳኔም እንደ ብርሃን ትደርሳለች፤ አሕዛብ በክንዴ ይታመናሉ፤ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ በክንዴም ይታመናሉ።
ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸውም አይጠፋም፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆናሉ።”
አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ፥ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በምድረ በዳ ፊት ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።
በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል፥ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፥ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም።
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”