Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 42:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፥ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 42:4
33 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ ይጠ​ሩ​ሃል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አክ​ብ​ሮ​ሃ​ልና ስለ አም​ላ​ክህ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ በአ​ንተ ይማ​ጠ​ናሉ።


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።”


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።


ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ይስጡ፤ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በደ​ሴ​ቶች ይና​ገሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የዘ​ነ​ጋሁ ሳል​ሆን፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌ​ላ​ቸ​ውን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ሕግ ለሌ​ላ​ቸው ሕግ እን​ደ​ሌ​ለው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።


ብቻ​ውን ጠቢብ ለሆ​ነው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይሁን፤ አሜን።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም።


አሁ​ንም አላ​ወ​ቅ​ህ​ምን? አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አም​ላክ፥ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ የፈ​ጠረ አም​ላክ ነው፤ አይ​ራ​ብም፤ አይ​ጠ​ማም፤ አይ​ደ​ክ​ምም፤ ማስ​ተ​ዋ​ሉም አይ​መ​ረ​መ​ርም።


ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምስ​ጋ​ና​ውን ያጸ​ድ​ቅና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መከረ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም ነገ​ሥ​ታት ተግ​ሣ​ጼን አድ​ም​ጡኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ ፍር​ዴም ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን ይሆ​ና​ልና።


ጽድቄ ፈጥና ትመ​ጣ​ለች፤ ማዳ​ኔም እንደ ብር​ሃን ትደ​ር​ሳ​ለች፤ አሕ​ዛብ በክ​ንዴ ይታ​መ​ናሉ፤ ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ በክ​ን​ዴም ይታ​መ​ናሉ።


እርሱ የም​ድ​ርን ክበብ ያጸ​ናል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩት እንደ አን​በጣ ናቸው፤ ሰማ​ያ​ትን እንደ መጋ​ረጃ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፥ እንደ ድን​ኳ​ንም ለመ​ኖ​ሪያ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፤


እጁ የሰለለችውንም ሰው “ተነሥተህ ወደ መካከል ና፤” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios