ልጆቹም ታውከው ይሰደዱ፥ ይለምኑም፥ ከቤቶቻቸውም ያባርሯቸው።
ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል?
ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፥ በፍልስጥኤም ላይ ድሌን ዐውጃለሁ።
አምላክ ሆይ! ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል?
አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ።