ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
እግዚአብሔርን ልክ ስለሌለው ፍቅሩ፣ ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤
ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥
ለሰው ልጆች ስላደረገላቸው ድንቅ ነገሮችና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ እግዚአብሔርን ያመስግኑ።
ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፤ አምላካችንም ጻድቅ ነው።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
ሰይፍህን ምዘዝ፥ የሚከብቡኝንም ክበባቸው ነፍሴን፦ ረዳትሽ እኔ ነኝ በላት።
ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ “መቼ ይሞታል? ስሙስ መቼ ይሻራል?” ይላሉ።
ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና መዘበቻ።
ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
ይህንም ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፤ በሚመጣውም ዘመን አያውቁትም።
ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥