Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 78:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ች​ንም ስድብ ሆንን፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ ሣቅና መዘ​በቻ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከልጆቻቸው አንሰውረውም፥ ለሚመጣውም ትውልድ የጌታን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት እንናገራለን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነዚህን ነገሮች ከልጆቻችን አንሰውርም፤ ስለ እግዚአብሔር ኀይል፥ ስላከናወናቸውም ታላላቅ ሥራዎችና ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ለተከታዩ ትውልድ እንናገራለን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:4
17 Referencias Cruzadas  

ጠቢ​ባን የተ​ና​ገ​ሩ​ትን፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ሰ​ወ​ሩ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝ፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።


ምስ​ጋ​ና​ውን ሁሉ እና​ገር ዘንድ፤ በጽ​ዮን ልጅ በደ​ጆ​ችዋ፥ በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል።


ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘ይህ ሥር​ዐት ለእ​ና​ንተ ምን​ድር ነው?’ ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ እና​ንተ፦


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤


በዚ​ያም ቀን፦ ‘ከግ​ብፅ በወ​ጣሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ስለ​አ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ነው’ ስትል ለል​ጅህ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ።


እኔ ዛሬ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ ሕያ​ዋን ብቻ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ ከዛሬ ጀምሮ ጽድ​ቅ​ህን የሚ​ና​ገሩ ልጆ​ችን እወ​ል​ዳ​ለሁ።


ይህን ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ንገሩ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለኋ​ለ​ኛው ትው​ልድ ይን​ገሩ።


ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


ለል​ጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ረው፤ በቤ​ት​ህም ስት​ቀ​መጥ፥ በመ​ን​ገ​ድም ስት​ሄድ፥ ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አስ​ተ​ም​ረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos