ደነገጡ፥ እንደ ሰካራምም ተንገዳገዱ፥ ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠ።
ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ።
ዘሮቻቸውን ሁሉ በአሕዛብ መካከል እንደሚጥላቸውና በመላው ዓለም እንደሚበታትናቸው ገለጠላቸው።
ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።
ዔ። የእግዚአብሔር ፊት ክፍላቸው ነበረ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፤ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።
ደግሞም ወደ አሕዛብ እበትናቸው ዘንድ፥ በሀገሮችም እበትናቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነርሱ ላይ እጄን አነሣሁ።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ወደ እነርሱ በሚወስድህ አሕዛብ መካከል ሁሉ የደነገጥህ፥ ለምሳሌና ለተረትም ትሆናለህ።