ለዘለዓለም እንዳትናወጥ፥ ምድርን መሠረታት፥ አጸናትም።
ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።
ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።
ሥጋውን እንደ ሕፃን ሥጋ ያለመልማል፤ ከሰዎችም ይልቅ ወደ ጕብዝናው ዘመን ይመልሰዋል።
ጨለማንም ላከ ጨለመባቸውም፤ ቃሉንም መራራ አደረጉት።
ካህን ሞዓብም ተስፋዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፤ ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ይቀበላል፥ ምሕረቱም ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ የሚያምንም የለም ይላሉ።
ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
ከዚያም የተገኘውን ገንዘብዋን እሰጣታለሁ፤ ምክርዋንም በአኮር ሸለቆ እገልጣለሁ፤ እንደ ሕፃንነትዋ ወራት፥ ከግብፅም እንደ ወጣችበት ቀን ትዘምራለች።
ስለዚህ አንሰልች፤ በውጭ ያለው ሰውነታችን ያረጃልና፤ በውስጥ ያለው ሰውነታችን ግን ዘወትር ይታደሳል።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ሙሴም በላከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬም ገና እንዲሁ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጽኑዕ ነኝ።