ሕጉን በሚጠብቁ፥ ትእዛዙንም ያደርጉ ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው።
ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።
ገና ያልተወለዱት ሰዎች እንዲያመሰግኑት ይህን እግዚአብሔር ያደረገውን ድንቅ ነገር ለሚመጣው ትውልድ ጻፉ።
በአፋቸው ሲወዱ፥ ራስዋ መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥
ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው።
እነርሱም ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርኋቸው ሕዝብ ናቸው፤
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ” እለዋለሁ።
ነገር ግን ይህ የተጻፈ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እናንተ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ የዘለዓለም ሕይወትን ታገኙ ዘንድ ነው።
የተጻፈው ሁሉ በመታገሣችንና መጻሕፍትን በመታመናችን ተስፋችንን እናገኝ ዘንድ እና ልንማርበት ተጻፈ።
እነርሱን ያገኛቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለምንነሣው ለእኛ ትምህርትና ምክር ሊሆነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።
እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ላዘጋጀው በጎ ሥራ በኢየሱስ ክርስቶስ የፈጠረን ፍጥረቱ ነንና።
ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።