ሐሰተኛ ምስክርን የሚያቀጣጥል፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።
በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምስክር፥ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው።
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የኀጢአተኛ እጅም አያውከኝ።
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
“ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል፤ የዐመፅ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከዐመፀኛ ጋር አትቀመጥ።
ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው።
የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።
ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።
ነፍሰ ገዳይን ከጉባኤ አውጣ፥ ከእርሱም ጋር ክርክር ይወጣል፥ በጉባኤ በሚቀመጥበት ጊዜ ሁሉን ያዋርዳልና።
ጠማማ ልቡ ሁልጊዜ ክፋትን ያስባል፤ እንደዚህም ያለ ሰው ጠብን በከተማ ላይ ይዘራል።
እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።
ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።
የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙም፤
የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስ ላይና በኦሪት ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤
ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤
የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።