እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።
ከተግሣጽ ጕድለት የተነሣ ይሞታል፤ ከቂልነቱ ብዛት መንገድ ይስታል።
አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥ በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።
ከመጠን በላይ በሆነው ሞኝነቱ መንገዱን ይስታል፤ ራሱን መቈጣጠር ካለመቻሉ የተነሣ ይሞታል።
ኃጥኣንን ግን አያድናቸውም እግዚአብሔርን ያዩ ዘንድ አይወዱምና፥ ሲገሥፃቸውም አይሰሙምና።
እፍ ብሎባቸዋልና ይደርቃሉ፥ ጥበብም የላቸውምና ይጠፋሉ።
ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።
የጻድቃን ከንፈሮች የሩቁን ያውቃሉ፤ ሰነፎች ግን በድህነት ይሞታሉ።
የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።
ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።
ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።