ምሳሌ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቼ ሆይ! የአባታችሁን ምክር ስሙ፤ በጥንቃቄ አዳምጡ፤ ማስተዋልንም ታገኛላችሁ። |
እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም ሚስቶቻችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም፤