እግዚአብሔር ጥበብን አስተማረኝ፥ የቅዱሳንንም ዕውቀት ዐወቅሁ።
በሰነፍ ሰው ዕርሻ በኩል ዐለፍሁ፤ በልበ ቢስ ሰው የወይን ቦታ ዐልፌ ሄድሁ፤
በሰነፍ ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ።
በሰነፍና ማስተዋል በጐደለው ሰው እርሻ ውስጥ በወይኑም አትክልት ቦታ ሄድኩኝ፤
“ስማኝ ልንገርህ፥ እነሆም ያየሁትን እነግርሃለሁ፤
እኔ እንዳየሁ፥ ኀጢኣትን የሚያርሱ፥ የሚዘሩአትም መከራን ለራሳቸው ያጭዳሉ።
እነሆ፥ ይህን ዐውቀን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፤ አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ ዕወቅ።”
ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ አእምሮ የጐደለውንም ሰው በበትር ይመታል።
ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።
የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።
አመንዝራ ግን በአእምሮው ጉድለት፥ ነፍሱ የሚጠፋበትን ጥፋት ይሠራል።
በሰዎች ስንፍናና ቦዘኔነት የቤት ጣራ ይዘብጣል፥ በእጆች ስንፍናም ቤት ያፈስሳል።
ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥእም በክፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከንቱ ዘመኔ አየሁ።